የኢትዮጵያ መንግሥት ድርቁን በይፋ አለማረጋገጡ እርዳታ አቅርቦት ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ አደጋ ያጋለጠውን ድርቅ በይፋ አለማረጋገጡ ዓለም አቀፍ እርዳታዎች እንዳይፋጠኑ እና የድርቅ ተጎጂዎች ተገቢውን እርዳታ በወቅቱ እንዳያገኙ እያደረገ ነው፤ ሲሉ የእርዳታ ተቋማትና ተንታኞች ተናገሩ።

ለሦስት ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቁ ባጠቃቸው አካባቢዎች 12 ሚሊዮን ሰዎች ለምግብ እጥረት፣ ለውሃ ጥም እና ለበሽታ የተዳረጉ ሲሆን ከ 4.5 ሚሊየን በላይ ከብቶችም ሞተዋል። ዘገባውን ከተያያዘው ፍይል ይከታተሉ።