የትግራይ ሕዝብን ከችግር ለመታደግ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያፈልግ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

የፌዴራል መንግሥቱና የህወሐት ዋና ተደራዳሪዎች ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ የሠላም ሥምምነት ከተፈራረሙና ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ የትግበራ ሠነድ ላይ ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ የተለያየ እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል እየደረሱ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች በመግለፅ ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የክልሉ የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ከሥምምነቱ ወዲህ ከ36 ሺሕ ኩንታል በላይ እህል ወደ ትግራይ መግባቱ ገልፀው ነገር ግን መጠኑ ከሚያስፈልገው በእጅጉ ያነሰ ነው ብለዋል።

የሕፃናት አድን ድርጅት የእርዳታ እህል በማድረስ ላይ ከሚገኙት ረድዔት ድርጅቶች አንዱ ሲሆን ከሥምምነቱ ወዲህ የተሻለ ሁኔታ በመፈጠሩ እርዳታ ለተጎጂዎች ማድረሱን ገልጿል። አሁንም ግን የበለጠ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁሟል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ /