ድሬዳዋ ላይ የተጀመረው የሳፋሪ ኮም አገልግሎት ደንበኞቹ አስተያየት

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው የግል ተቋም ደንበኛች አገልግሎቱን እየተጠቀሙ ነው። ሳፋሪኮም የተባለው ይሄው የመጀመሪያ የግል ተቋም የሙከራ አገልግሎቱን በቅድሚያ የጀመረው በድሬዳዋ ነው።

ባለፈው ሰኞ የተጀመረው አገልግሎት ከኢትዮ-ቴሌኮም ወደ ሳፋሪኮም ሲደወል ከሚያጋጥመው ችግር በስተቀር በተሳካ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ደንበኞች ተናግረዋል።

የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች የቀረቡበት ዋጋም ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር ተቀራራቢ መሆኑን የሳፋሪ ኮም መግለጫ ያመለክታል።

አዲስ ቸኮል የሳፋሪኮምን የመጀመሪያ ደንበኞችን አነጋግሯል።