እርዳታ በመግባትና ባለመግባቱ ጉዳይ መንግሥትና ህወሓት ተለያይተዋል

Your browser doesn’t support HTML5

ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እየገባ ባለበት ሁኔታ ላይ የፌዴራል መንግሥቱና የህወሓት ዋና ተደራዳሪዎች የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን “እርዳታ ያለአንዳች ገደብ እንዲገባ እየተደረገ ነው” ሲሉ፤ የህወሓቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ “ሬድዋን ያሉት ሙሉ በሙሉ ሃሰት ነው፤ ምንም በሌለበት ነው የሚናገሩት” ብለዋል።

በሌላ በኩል ፀብ በማቆም ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ በፌዴራሉ መንግሥትና በህወሓት ከፍተኛ አዛዦች መካከል ናይሮቢ ውስጥ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።