“ተወልደ ለኢትዮጵያም አፍሪካም ባለውለታዋ ነው” – የዶ/ር ተወልደብርሃን ወዳጆች

Your browser doesn’t support HTML5

በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የብዝሀ ሕይወት እና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ተመራማሪ ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር ሕይወት ማለፍ ሐዘኑን የገለፀው የግለታሪካቸው ጸሐፊ ዘነበ ወላ፤ “በሀገሩ፣ በወገኑ እና በራሱ ማኅበረሰብ ጥሩ አስተዋፅኦ ካደረጉ እና ተጠቃሽ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው፡፡ ዓለም ለወደፊት ስለ አካባቢ ጥበቃ አሳቢዎቿ በምትፅፍበት ጊዜ ከአውራዎቹ አንዱ ዶ/ር ተወልደ ይሆናል፡፡” ብሏል።