በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት አትሌቲክስ ቡድን

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለተኛ ሆና እንድታጠናቀቅ ያስቻሉት አትሌቶች እና የቡድኑ አባላት በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በተዘዋወሩበት ወቅት ከሕዝቡ ከፍተኛ አድናቆት ጠብቋቸዋል፡፡

በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረው የአቀባበል ሥነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረገች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፤ ከትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸውን የሚያገኙበት ዕድል እንዲፈጠር ጠይቃለች፡፡

በውድድሩ ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ ተበርክቶላቸዋል፡፡

/በኬኔዲ አባተ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/