ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ድጋፉን በዋና አስተባባሪነት እያሰባበሰበ የሚገኘው የጉዞ አድዋ አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ፤ ከትናንት ጀምሮ በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውንና ገልጿል። ኅብረተሰቡም ድጋፍ በማቅረብ እየተሳተፈ መሆኑን ተናግሯል።

የኅብረተሰቡ ምላሽ አበረታች መሆኑን የገለጸው ሌላው አስተባባሪ ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ በበኩሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለሌሎች አካባቢዎችም ኮንሰርት ማዘጋጀትን ጀምሮ በተለያየ መልኩ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራው እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች ለቀረበው የድጋፍ ጥሪ ከግለሰብ ጀምሮ የተለያዩ አካላት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በተያያዘ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ከተለያዩ እህት ማኅበራት ጋር በመተባበር በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን የማኅበሩ ዋና ጸኃፊ ጌታቸው ታዓ ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡