እየከፋ ለመጣው የአፍሪካ ቀንድን ላጠቃው ድርቅ አፋጣኝ እርምጃ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

“በምስራቅ አፍሪካ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ እየተሰቃዩ ባሉባቸው አካባቢዎች ‘ድርቁ ከቸነፈር ደረጃ ደርሷል’ የሚለው እስኪታወጅ መጠበቅ ሳይሆን አሁን ነው ለጋሾች ሕይወት ለመታደግ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው” ሲሉ የዓለም አቀፉ የነፍስ አድን ኮሚቴ - አይአርሲ ኃላፊ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ፣ የኬንያ እና የሶማሊያ አካባቢዎች ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በአካባቢው ከታየው ሁሉ እጅግ ለከፋ ድርቅ መጋለጣቸውን ተከትሎ የሶማሊያ ከፊል አካባቢ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳመለከተው ድርቁ ከቀድሞውም ወደ ከፋ የቸነፈር ደረጃ መድረሱ ሊታወጅ ነው።

የአይአርሲ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሚሊባንድ በቪዲዮ አማካኝነት በሰጡት በዚህ አጭር መግለጫ ሲናገሩ "እርምጃ ለመውሰድ ሁኔታውን በርቀት ሳይሆን ፊት ለፊት በማየት አሁኑኑ ነው ማድረግ ያለብን” ብለዋል።