ሕይወታዊ ተልዕኮ ያነገበው ሽሽጉ የዋሽንግተን ዲሲ ብሔራዊ የዕፀዋት መዘክር

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የዕፀዋት መዘክር(US National Arboretum) በዋሽንግተን ዲሲ ጎዳናዎች መሀከል የመቆሙን ያህል፣ ከእይታ የተሰወረ ያህል በብዙዎች ሳይታወቅ የሚገኝ ግዙፍ የዕፀዋት ምርምር እና መናፈሻ ነው፡፡
የዕፀዋት መዘክሩ፣ 183 ሄክታር ስፋት እና እጅግ ብዛት ያላቸው የአበባ እና የዛፍ ዐይነቶችን የያዘ ሥፍራ ሲኾን፣ ወሳኝ ሳይንሳዊ ምርምሮች ይከናወኑበታል፡፡

የአሜሪካ ድምፅዋ ዶራ መኩዋር፣ ብሔራዊ የዕፀዋት መዘክሩ እና መናፈሻው፣ ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ተልዕኮ አኳያ፣ ያለውን ወሳኝ ቦታ የሚያስቃኝ ዘገባ አሰናድታለች፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡