የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ፍ/ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክርነት ሰጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶር.)፣ በዛሬው ዕለት፣ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው፣ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዲሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው የክሥ መዝገብ ላይ የመከላከያ ምስክርነት ሰጡ፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ፣ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ድርጅት፣ ሁለት መርከቦችን በመግዛት ቆራርጦ እንዲጠቀምባቸው በቦርድ መወሰኑን እንደሚያውቁ፣ በሰጡት የምስክርነት ቃል ተናግረዋል።

መርከቦቹን ከነበሩበት ለማንቀሳቀስም፣ ለኮርፖሬሽኑ ጊዜያዊ ፈቃድ ተሰጥቶት እንደነበር እንደሚያውቁ ገልጸዋል።