ካመሩን ውስጥ ጎርፍ ህይወት አጠፋ

Your browser doesn’t support HTML5

ካመሮንና ናይጄሪያ በዋሰኑበት የድንበር አካባቢ የደረሰ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ በጥቂቱ ስድስት ሰዎችን ገድሏል።

ጎርፉ መኖሪያ ቤቶችን መውሰዱንና ለውጭ ገበያ የተዘጋጀ በብዙ ሺህ ቶን የሚገመት ምግብ ማውደሙን የካመሩን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ወደ አካባቢው የሚያደርስ ትራንስፖርት በመቋረጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መውጫ ማጣታቸውና ፈጥኖ ጥቅም ላይ መዋል የነበረበት ምርት መበላሸት መጀመሩንም አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች ተናግረዋል።

ሞኪ ኤድዊን ኪንድዜካ ከያውንዴ ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።