የቦረና ድርቅ ተጎጂዎች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎችን ለመርዳት በልዩ ልዩ ግለሰቦች እና ተቋማት እየተደረገ የሚገኘውን የድጋፍ ማሰባሰብ ያደነቁት የድርቅ ተፈናቃዮች፣ እርዳታው በቶሎ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ፣ የተሰበሰበውን እርዳታ በፍጥነት የሚያደርስ ኮሚቴ ማቋቋሙን ገልጾ፣ ለዚኽም ጥናት ሲያካሒድ መቆየቱን አስታውቋል።

በአንጻሩ እርዳታ ፈላጊዎቹ፣ ችግራቸው ጊዜ የማይሰጥ በመኾኑ በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡