በድርቅ እና የጸጥታ ችግር የተባባሰው የኮሌራ ወረርሽኝ በኦሮሚያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እየተዛመተ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በድርቅ በተጠቁት እና የጸጥታ ችግር ባለባቸው በኦሮሚያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች፣ የኮሌራ ወረርሽኝ አሁንም እየተዛመተ እንደኾነ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ገመቹ ሹሚ፣ ወረርሽኙ፥ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር፣ በባሌ ዞን ከተከሠተ ወዲህ፣ የ81 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ጠቅሰው፣ አሁን ደግሞ፣ በድርቅ በተጠቁ የክልሉ ዞኖች ውስጥ እየተዛመተ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሽታው፣ በቦረና ዞን ከዱብሉቅ ከተማ በቅርብ ርቀት ወደሚገኘው የተፈናቃዮች መጠለያ መግባቱንም፣ የዱብሉቅ ወረዳ አስተዳደር ባልደረባ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ በበኩሉ፣ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር፣ ድርቅ እና የጸጥታ ችግሮች ዕንቅፋት እንደሆኑበት ይናገራል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።