ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ መቸገራቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን በሎ ጀገንፎይና ሴዳል ወረዳ ውስጥ ተፈናቅለው በክልሉ ውስጥ እንዲሁም በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች “ድጋፍ እየተደረገልን አይደለም"ሲሉ አመለከቱ።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የመንገድ መዘጋጋት እንደነበር ገልፀው፤ ከሰኔ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ድጋፍ የጫኑ መኪኖች መንገድ ላይ በመቆማቸው የተፈጠረ ችግር መሆኑን ተናግረዋል።