ንግድ ባንክ በትግራይ የሂሳብ ሥራ ማጠናቀቁን ገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ቅርንጫፎች ሲያከናውን የቆየው የሂሳብ ሥራ ማጠናቀቁን የትግራይ አስቸኳይ መልሶ ማቋቋም ሥራዎች ማስተባበሪያ አስታወቀ፡፡

የማስተባበሪያው ምክትል ሰብሳቢ አቶ አበበ ገብረህይወት የሂሳብ ሥራው መጠናቀቅ በክልሉ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለማስጀመር ዕድል ይሰጣል ብለዋል፡፡

የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ሥራ የጀመሩት ባንኮች የብር እጥረት እንዳለባቸው ገልፀው ባንኮቹ አገልግሎት እንደማይሰጡ ተናግረዋል፡፡

ባንክ ውስጥ የሚገኝ ገንዘባቸውን መጠቀም ባለመቻላቸው ለችግር መዳረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡