የናይሮቢው የአፍሪካ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ዓመታዊ የልምድ ልውውጥ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፍሪካ ውስጥ እና ከአፍሪካ ውጪ ያሉ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች የተሳተፉበት ዓመታዊ የሥልጠና እና የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር፣ በቅርቡ ናይሮቢ ውስጥ ተካሒዷል፡፡

ዓመታዊውን መርሐ ግብር ያዘጋጀው፣ ቢሮው በኒው ዮርክ የኾነው “የሙሉዓለም የሥራ ፈጠራ ድርጅቶች ማዕከል”(Center For Global Enterprises) የተባለ ተቋም ነው፡፡ የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች፣ የንግድ ሥራዎቻቸውን ለማሻሻል እና ለማሳደግ ስለሚችሉበት መንገድ፣ ከዘርፉ አዋቂዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

የቪኦኤዋ ማርያማ ዲያሎ ተከታትላዋለች፡፡