የአፍሪካ የጸረ-ሙስና ጉባኤ በጋቦሮኔ

Your browser doesn’t support HTML5

ቦትስዋና በትናንትው እለት እና ዛሬ በአፍሪቃ ኅብረት እና በዓለም የገንዘብ ድርጅት /አይኤምኤፍ/ የተመራ የፀረ ሙስና ጉባኤ አስተናግዳለች።

"የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመልካም አስተዳደር አስፈላጊነትን ይበልጥ አጉልቶ አሳይቷል" ሲል አይኤምኤፍ ጉባኤው አስታውቋል።

ጠንካራ የኢኮኖሚ ተቋማት ያላቸው አገሮች አዳዲሶቹን ፈተናዎች ለመቋቋም የተሻለ እድል እንዳላቸው እና ፈጥነው ለማገገምም ዝግጁ መሆናቸውም አይኤምኤፍ ጨምሮ አመልክቷል።