ጎርፍ አፋር ውስጥ ህይወት አጠፋ

Your browser doesn’t support HTML5

የክረምቱ ዝናብ በአፋር ክልል ሎጊያ አካባቢ ባስለተለው ጎርፍ 13 ሰዎች መሞታቸውን የዐይን እማኝ ነን ያሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አይሳኢታ ወረዳ ውስጥ ደግሞ ከ4 ሺህ 200 በላይ አባዎራ መፈናቀሉን የወረዳው የእንስሣት፣ የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ፅህፈት ቤት ቢያስታውቅም እስካሁን የተደረገላቸው ድጋፍ እንደሌለ ተፈናቃዮቹ ገልፀዋል።

ኤሊድአር ወረዳም ላይ የተከማቸው የጨው ምርት በጎርፍ ወሰዱን ወረዳው አመልክቷል።

አደጋን የመከላከልና የዝግጅት ሥራ አለመከናወኑን አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የክልሉን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርና የምግብ ዋስትና ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ቪኦኤ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካም።