አዲሱ “ምስራቅ ቦረና ዞን” የቀሰቀሰው ተቃውሞ

Your browser doesn’t support HTML5

“ምስራቅ ቦረና ዞን” የሚል ስያሜ የተሰጠውን አዲስ ዞን ለማዋቀር የተደረሰበት ውሳኔ ሕዝብ እንዳልመከረበት የገለፁት የጉጂ አባገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

በጉጂ ዞን ውስጥ የሚገኘው የኔጌሌ ከተማ የአዲሱ የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማ እንዲሆን መወሰኑን ጨምሮ በውሳኔው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በተመለከተ ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውንም አመልክተዋል።

አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ከክልሉ ባለሥልጣናት ጋራ በመከሩበት ወቅት የተሰጣቸውን መልስ እንደማይቀበሉ ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።