የባሌ አባገዳዎች ተቃውሞ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መዳ ወላቡ የተባለው ቦታ “የኦዳ ሮባ መገኛ እና የስኮ እና መንዶ መቀመጫ በመሆኑ ወደ ምስራቅ ቦረና መካለል የለበትም” ሲሉ አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቤቱታ አሰሙ።

ቅሬታቸውንም ለፌዴራል እና ለኦሮሚያ ክልል መንግሥት ማቅረባቸውን የገለፁት አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከመንግሥት አካላት መልስ እየተጠባበቁ እንደሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዲህ ያለ አደረጃጀት በየጊዜው እንደ አስፈላጊነቱ ይከናወናል ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የጉጂ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በቅርብ ጊዜ ለፌዴራል እና ክልል መንግሥት ጥያቄ አቅርበው የዞን አደረጃጀቱ እንደማይቀለበስ ከመንግሥት ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡