የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር እንሠራለን አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በትብብር በመስራት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጹ።

ሁለቱ አካላት፣ ሀገራዊ ምክክሩን ጨምሮ የጋራ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ መለሰ ምክር ቤታቸው ከኮሚሽኑ ጋር ተቀራርቦ መሥራት እንደጀመረ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባፌም እንዲሁ ምክር ቤታቸው ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ሆኖም በኮሚሽኑ አባላት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አንጸባርቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ማክሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ፣ ሁሉም አካላት ኮሚሽኑን በቅንነት እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡