ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ተከራይተው በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሠማሩ የሕንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት እና በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸውን ሚና የፈተሸ መድረክ ሕንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ላይ ከጥር 28 እስከ 30 / 2005 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ተካሂዷል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ተከራይተው በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሠማሩ የሕንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት እና በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸውን ሚና የፈተሸ መድረክ ሕንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ላይ ከጥር 28 እስከ 30 / 2005 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ተካሂዷል፡፡
ስብሰባው የተዘጋጀው ዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ በሚገኘው የሃሣብ ጉባዔ ቡድን /Think-tank Group/ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ሲሆን ሕንዳዊያን የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች - የሕንድ ማኅበራዊ ተግባር መድረክ፣ ካልፓቭሪክሽ የሚባለው የሕንድ የተፈጥሮ አካባቢና የመብቶች ተሟጋች ቡድን እና የማኅበራዊ ልማት መድረክ ተባብረውበታል፡፡
“ያልተሰሙ ድምፆች” የሚል ሠነድ የወጣበት ይህ ስብሰባ የኢትዮጵያና የሕንድን የመሬት ባለቤትነት መብቶች መመልከቱን የኦክላንድ ኢንስቲትዩት መሥራችና ዋና ዳይሬክተር አኑራድሃ ሚታል ገልፀዋል፡፡
መድረኩ ውይይቶች የተካሄዱበት፣ የምሁራንና የተመራማሪዎች ሃሣቦች የተሰሙበት፣ የቀድሞ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገኙበት፣ ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠበት፣ የሕዝቦች ንቅናቄዎች እና የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች የተናጋሩበት ነበር፡፡
የሕንድ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች በሃገራቸው ውስጥ እና በውጭም ያካሂዱታል የተባለውን - በኦክላንድ ኢንስቲትዩት አጠራር “ሕገ-ወጥ” እና “ምግባረ-ወጥ” የሆነውን የመሬት ይዞታ አካሄድ “… አሣንሶ የማየት ወይም ችላ የማለት ወይም ሆን ብሎ የመረጋገጥ …” የኢንዱስትሪ አካሄድ ያለውን የልማት አቅጣጫ ለመተቸትና ለመፈተሽም ዕድል ተከፍቷል፡፡
ቀደም ሲልም መጥቶ የነበረ የኦክላንድ ኢንስቲትዩት ጥናት ሪፖርት ግዙፍ አቅምና ስፋት ያላቸው ዓለምአቀፍ ኩባንያዎች ወደአፍሪካ ለመግባት የያዙትን አዲስ አቅጣጫ ማመላከቱን ኢንስቲትዩቱ አመልክቷል፡፡
የኒው ደልሂው መድረክ ታዲያ ሕንዳዊያኑ ኩባንያዎች በራሣቸው ሃገር ውስጥና በውጭም በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬቶችን ለማግኘት የሚፈርሟቸውን ውሎች የሚይዙባቸውን ስልቶች ወይም ስትራተጂዎች ምንነት ገላልጦ መክሯል፡፡
በጉባዔው ላይ ተገኝተው ከተናገሩ ተጋባዦች መካከል “የአኝዋ ሕልውና ድርጅት” የሚባለው ቡድን ዳይሬክተር አቶ ኚካው ኦቻላ እና የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚባለው ቡድን መሪ ኦባንግ ሜቶም ይገኙባቸዋል፡፡
ሁለቱም ሰዎች መሠረታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ሕንዳዊያኑ ኩባንያዎችና ኢንቬስተሮች የተስፋፉ መሬቶችን ይዘውበታል የሚባለው የጋምቤላ ክልል ነው፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፤ ዝርዝር ይዟል፡፡