አጎአ አዲስ አበባ ላይ ይሰበሰባል

  • እስክንድር ፍሬው
    ሔኖክ ሰማእግዜር
አጎአ

አጎአ

ዩናይትድ ስቴትስ ከሠሃራ በስተደቡብ ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች የከፈተችው የዕድገትና የገበያ ተጠቃሚነት ዕድል - አጎአ 12ኛ ጉባዔ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ ይጀመራል፡፡




አጎአ

አጎአ


Your browser doesn’t support HTML5

አጎአ አዲስ አበባ ላይ ይሰበሰባል


ዩናይትድ ስቴትስ ከሠሃራ በስተደቡብ ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች የከፈተችው የዕድገትና የገበያ ተጠቃሚነት ዕድል - አጎአ 12ኛ ጉባዔ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ ይጀመራል፡፡

አጎአ ከገበያ ዕድል በተጨማሪ ሌሎች የንግድ መሰናክሎችንም ማስወገድ እንዲችል አፍሪካዊያን ተሣታፊዎች እንደሚጠይቁ አንድ የአስተናጋጅዋ ሃገር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታውቀዋል፡፡

በጉባዔው ላይ በርካታ ተሣታፊዎች እንደሚገኙም የኢትዮጵያ የንግድ ሚኒስቴር የንግድ ግንኙነቶች ተደራዳሪ አቶ ገረመው አያሌው ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
አጎአ

አጎአ


በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ገበያ በአጎአ የቀረጥና ታሪፍ ነፃ ስምምነት መሠረት የምትልከው ምርት መጨመሩን የዩናይትድ ስቴትስ የግንድ ወኪል ዩኤስዲአር አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ላይ ከሚካሄደው የአጎአ ጉባዔ አስቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ረቡዕ፤ ሐምሌ 24/2005 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጎአ ዕድሉን ቢከፍትም ብዙ ሥራ እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ለዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡