አፍሪካውያን ስደተኞች በየመን

Your browser doesn’t support HTML5

ከ6 መቶ 50 በላይ የአፍሪካ ስደተኞች በደቡባዊ የመን ባህር ጠረፍ ላይ በምትገኘው አደን ከተማ በርሃብና በውሃ ጥም በመሰረታዊ ፍላጎቶች እጦት በእስር እየተሰቃዩ ነው፡፡ እነዚሁ ተስፋ የቆረጡ፣ የተራቡና የተጨነቁ አፍሪካውያን ስደተኞች በደቡባዊ የመን በአድን ከተማ /መጋዘን/ በሚመስል እስር ቤት ውስጥ ተከማችተዋል፡፡ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ የተሰደዱና ተስፋ የቆረጡ፣ አድካሚና አስልቺ ጉዞ አድርገው አሁን ያሉበት ስፍራ የደረሱ ናቸው፡፡