አፍሪካውያን ፍልሰተኞች

Your browser doesn’t support HTML5

በሜድትራንያን ባህር በጎማ ጀልባዎች ላይ የነበሩ 60 ፍልሰተኞችን ያሳፈረው ስደተኞቹን ከሞት ለማትረፍ የሚጥረው መርከብ ማልታና ኢጣልያ አላስገባ ካሉት በኋላ ትላንት በስፔን ወደብ ገብቷል። በያዝነው አመት በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች በአውሮፓ ጠረፎች ላይ ደርሰዋል። ደቡባዊ የአውሮፓ ሀገሮች ሌሎቹም ሸክሙን ካልተጋሩ በስተቀር በአሁኑ ወቅት የገቡትን ፍልሰተኞች አንቀበልም እያሉ ነው።