የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች 138 ፍልሠተኞች ባህር ከመስጠም መዳናቸውን አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ተነስተው ከቶሪሊ በስተደቡብ ብዙ ኪሎ ሜትሮች ከተጓዙ በኋላ ነበር ይጓዙበት የነበረ ጀልባ ሞተሩ በመጥፋቱ እና ሥራውን በማቆሙ ለመጠገን እየሞከሩ ባለበት ሠዓት የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የደረሱላቸው፡፡ መርከቡ ወደ ደቡባዊ ጣሊያን እየተጓዘ የነበረ ሲሆን በጀልባው ተጭነው የነበሩ ስምንት ሴቶች ጨምሮ በርካታ ፍልሠተኞች ከአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ናቸው፡፡