አፍሪካ ነክ ርእሶች

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ባለፈው አርብ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው በዩክሬኑ ጦርነት እና አፍሪካ ላይ ስላስከተለው አንድምታ ተነጋግረዋል። ጦርነቱን ተከትሎ የእህል አቅርቦት መቋረጡ በበርካታ የአፍሪካ ሀገሮች የምግብ ዕጥረቱን አባብሶታል በሚሊዮኖች የተቆጠሩ አፍሪካውያን ለረሃብ ተጋልጠዋል፣ መሀመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ዘግቦበታል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ በቅርቡ ጋና ውስጥ ባካሄደው ዐመታዊ ስብሰባ የዩክሬይኑ ጦርነት የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያቀዛቅዝ መጠቆሙን የሚያመለክት ዘገባም ኬንት ሜንሳህ ከአክራ አጠናቅሯል ቆንጅት ታየ ሁለቱን አጣምራ ለአፍሪካ ነክ ርዕሶች ወደ አማርኛ መልሳዋለች።