ጆሃንስበርግ - ደቡብ አፍሪካ —
ምሥራቅና በደቡባዊ አፍሪካ ሃገሮች ውስጥ በኤድስ ላይ ተጨብጧል የሚባለውን ግዙፍ ስኬት የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መርኃግብር ባለሥልጣናት አሞግሰውታል፡፡
ከኤድስ ጋር የተያያዘው የሞት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን እና ለኤችአይቪ እየተጋለጠ ያለው ሰው ቁጥርም በብዙ እየወረደ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ጠቁሟል፡፡
ይህ ክስተት መድኃኒት በብዛት የመገኘቱ ውጤት ነው የሚለው ይህ ሪፖርት ፈተናዎቹ ግን እንዳሉ እንደሚቀጥሉ አሳስቧል፡፡
ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው ዛሬ ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ላይ በተካሄደው የአህጉሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከጋምቤላ በስተቀር በብዙ የሃገሪቱ ክፍሎች የኤችአይቪ ሥርጭት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ ተናግረዋል፡፡
ለዝርዝር ዘገባው የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5