አፋር ውስጥ ተይዘው የቆዩት የትግራይ ተወላጆች ወደ መኖሪያቸው መመለስ ጀመሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “ህገወጥና የዘፈቀደ እሥራት” ሲል በጠራው ሁኔታ አፋር ክልል ውስጥ ሰመራ አጋቲና ውስጥ ተይዘው የቆዩ የትግራይ ተወላጆች ተለቅቀው ወደ አብአላና ሌሎችም የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው መመለስ መጀመራቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

ሰዎቹን ወደየመኖሪያቸው የመመለሱ ሥራ በ15 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ተመላሾቹ ንብረታቸው በጦርነቱ በመውደሙ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል።

ተይዘዋል የተባሉት ዘጠኝ ሺህ እንደሚሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሲገልፅ የአፋር ክልል መንግሥት ግን ሰዎች 7 ሺህ 800 መሆናቸውን አመልክቷል።