በአፋር ክልል ሠላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

Your browser doesn’t support HTML5

በቅርቡ በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ኦብኖ አከባቢ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ እናወግዛለን የሚሉ የክልሉ ኗሪዎች ትናንትናና ዛሬ የክልሉ ርዕሰ መዲና ሰመራን ጨምሮ በተለያዩ ከተማዎች ትእይንተ ህዝብ አካሄዱ፡፡ ኗሪዎቹ ቀጠናውን የትርምስ ማአከል ለማድረግ የሚሰሩ ሸፍጦችን መንግሥት በንቃት እንዲከላከል ጠይቀዋል፡፡