በጦርነቱ ምክኒያት የፍትህ ሥርዓት እንደተስተጓጎለበት አፋር ክልል አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክኒያት የፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሙሳ አብዱላሂ እንደ አዲስ ባገረሸው ጦርነት ምክኒያት ሁለት ዳኞች መገደላቸውን፣ ሰነዶችና መዛግብት መውደምና መጥፋታቸውን ተናግረዋል። ለዚህም ህወሓትን ተጠያቂ አድርገዋል። ስለ ሰነዶች መጓደልና የፍትሕ ሂደት የያዙ መዛግብት መጥፋትን ብተመለከተ ከህወሃት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

በሌላ በኩል የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት በአፋር ክልል ደርሷል ያሉትን ጉዳት በተመለከተ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እያሳወቅን ነው ብለዋል።