ደሴ —
አፋር ክልል ውስጥ ከጦርነት ሸሽተው ጋሊኮማ መጠለያ ተጠልለው በነበሩ ተፈናቃይ ሲቪሎች ላይ የክልሉ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ህወሓት አደረሰው ባሉት ባለፈው ሃሙስ በተፈፀመ ጥቃት ከሞቱት ከ200 በላይ ሰዎች 50 የሚደርሱት አስከሬናቸው እስካሁን አለመገኘቱን የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ አስታውቋል።
ከ50 በላይ ሰዎችም ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተሰጣቸው ነው መሆኑ ተገልጿል።
ጥቃቱና የደረሰውም ጉዳት በእጅጉ እንዳሳዘነው የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት የአጣዳፊ እርዳታ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ አስታውቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ሄንሬየታ ፎር ያወጡት መልዕክት በእጅጉ አሳሳቢ እንደሆነ ዛሬ ባወጡት ትዊት የገለፁት የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት የትግራይ መንግሥት መምከኑንና በክልሉ ሥልጣኑ የጊዜያዊ አስተዳደሩ መሆኑን የሚናገሩበት መቀሌ የሚገኘው “የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ህወሓት መር ባለሥልጣን አማካሪ መሆናቸው የሚነገረው ጌታቸው ረዳ አግባብ ካለው ምርመራ ከሚያካሂድ አካል ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5