የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የአፋር ክልል ተወላጆች አርብ ዕለት ዋሺንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል ። በተመሳሳይ ከትላንት በስቲያ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዎ የሚኖሩ የአማራና የአፋር ብሄር ተወላጆች ፣በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በብሄሩ ተወላጆች ላይ እየደረሱ ናቸው ያላቿው ጥቃቶች ሲፈጸሙ መንግሥት ቸልታ አሳይቷል በሚል ወቀሳ አሰምተዋል። በሌላ በኩል የትግራይ ተወላጆች በብራስልስ ተቃውሞ አሰምተዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የአፋር ክልል ተወላጆች ከትላንት በስቲያ ዕለት ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

አምስት ያህል የክልሉ ወረዳዎች በህወሓት ኃይሎች መያዛቸውን፣ ንጹሃንን በእጅጉ የጎዳ የከባዳ መሳሪያ ጥቃት እየተፈጸመባቸውም መሆኑን የጠቀሱት ሰልፈኞች ፣"የኢትዮጵያ መንግሥት የክልሉን ነዋሪዎች ደህንነት መጠበቅ ተስኖታል"በሚልም ወቅሰዋል ።

በተመሳሳይ ከትናንት በስቲያ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በተደረገ ሌላ ሰልፍ ላይ፣ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዎ የሚኖሩ የአማራና የአፋር ብሄር ተወላጆች ፣በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በብሄሩ ተወላጆች ላይ እየደረሱ ናቸው ያላቿውን ጥቃቶች በማንሳት፣ " ዘር ማጥፋት " ሲሉ የጠቀሱት ወንጀል ሲፈጸም የሀገሪቱ ፌዴራል መንግስት እና የክልል መንግስታት ቸልታ አሳይተዋል በሚል ወቀሳ አሰምተዋል።

በሌላ በኩል በአውሮጳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በበኩላቸው፣ የክልሉ ነዋሪዎች መሰረታዊ ግልጋሎቶችን እንዳያገኝ ሆን ብሎ ከልክሏል ያሉትን የኢትዮጵያን መንግስት ለመቀዋም - የአውሮፓ ህብረት አመራሮችንም ለማሳሰብ አደባባይ ወጥተዋል።