በጸጥታ ችግሮች የመንገዶች መዘጋት የበዓል ግብይቱን ማናሩን ነጋዴዎች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐዲስ አበባ ከተማ በበዓል ግብዓቶች ላይ፣ እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ መታየቱን፣ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ሸማቾች ገለጹ፡፡

የበዓል ግብይት እየተካሔደባቸው በሚገኙ የከተማዋ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ተዘዋውረን ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች፣ የግብዓቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን መናሩን ገልጸዋል፡፡

ነጋዴዎች በበኩላቸው፣ ከጸጥታ ችግሮች ጋራ በተያያዘ የሚስተዋሉ የመንገድ መዘጋቶች፣ በግብዓቶቹ አቅርቦት ላይ ያስከተሉት እጥረት የዋጋ ንረቱ አንዱ መንሥኤ ነው፤ ይላሉ፡፡

የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መኾኑን የገለጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ በሚያስገኙ አማራጮች ላይ እንዲሠራ ጠይቀዋል፡፡

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።