አለም አቀፍ ታዛቢዎች እንዲገቡ የአፍሪካ ህብረት ጠየቀ

  • እስክንድር ፍሬው
የኢትዮጵያ መንግሥት በተቃውሞ ሰልፎች ወቅት ተፈጸሙ ለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሙሉ በሙሉ እንዲያጣራ ወይም ለአህጉራዊና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያልተገደበ የማጣራት ፍቃድ እንዲሰጥ የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብት ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

በነዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ግጭቶች ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው የተሟላ ካሳ እና ማቋቋምያ ማግኘታቸውን እንዲያረጋግጥም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጠው ምላሽ ሁኔታውን ለማጣራት አህጉራዊም ሆነ አለምአቀፍ ቡድኖች እንደማይጋበዙ ይፋ አድርጓል።

የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው መግለጫ በመሰል አለምዓቀፍ ተቋማት የቀረቡ ጥሪዎች የደገመ እና ያጠናከረ ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አለም አቀፍ ታዛቢዎች እንዲገቡ የአፍሪካ ህብረት ጠየቀ