እነአቡበከር የክሥ መቃወሚያ አቀረቡ፤ የእነአንዱዓለም ይግባኝ ቀረበ፤ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለተመድ ግብረኃይል ገባ

Freedom Forum





የኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ማኅበረሰብን ጥያቄ እንወክላለን የሚሉት እነ አቡበከር አህመድ ሞሃመድ አቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ክሥ ተቃወሙ።

ጉዳያቸው የቀረበለት ፍርድ ቤት የማየት መብት እንደሌለው ገለፁ።

በእነ አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ የክሥ መዝገብም የይግባኝ አቤቱታ ቀርቧል።

አንዱዓለም አራጌ


በከፍተኛው ፍርድ ቤት በሽብር ፈጠራና ብሔራዊ ጥቅምን አሣልፎ በመስጠት ወንጀለኛ ያላቸውን ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች አቤቱታ አቃቢ ህግ መልስ እንዲሰጥበት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍሪደም ናው


በሌላ በኩል ለህሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው “Freedom Now” የሚባለው ድርጅት የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል ማቅረቡ ታወቀ።

እስክንድር ነጋ


ግብረኃይሉ በቀረበለት መመልከቻ ላይ በመጭው ሚያዝያ ውሣኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የድርጅቱን ሥራ አስኪያጅ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ አዲስ አበባ ላይ አነጋግሯቸዋል።

ዘገባዎቹን ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የእነአቡበከር የክሥ መቃወሚያ፤ የእነአንዱዓለም ይግባኝ፤ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለተመድ...