በጥቁር ልብስ ምክኒያት ከሥራ የታገዱ ሰዎችን ጉዳይ የቤተክርስቲያኒቷ ሕግ ቡድን እየተከታተለው ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ጋራ በተያያዘ ከሥራ የታገዱ ሠራተኞችን ጉዳይ እየተከታተለ እንደሚገኝ የቤተክርስቲያኗ የሕግ ቡድን አስታወቀ።

ከታገዱ ሠራተኞች መካከል አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የሰጡ አንዲት ግለሰብ፣ መፍትሔ ካላገኙ ቤተሰባቸው ለችግር እንደሚጋለጥባቸው ተናግረዋል፡፡

የቤተክርስቲያኗ የሕግ ቡድን አባል ዲያቆን ዘካሪያስ ወዳጅ፣ በሥራቸው ላይ ችግር የተፈጠረባቸውን ሰዎች እያገኙ በማናገር ላይ መሆናቸውንና ችግሩ በአስተዳደራዊ መንገድ ካልተፈታ ወደ ሕግ እንደሚወስዱት ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ፖሊስ ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ኅብረተሰቡን ለሽብር በማነሳሳት ወንጀል ጠርጥሪያቸዋለሁ ያላቸውን መምህር ምህረተአብ እና ወ/ሪት ፌቨንን ጨምሮ በእነርሱ መዝገብ ስር የነበሩ ሌሎች ሦስት ተጠርጣሪዎችን ከእሰስር መልቀቁም ታውቋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።