"ስለ ኮቪድ 19 ያወኩት ከአማዞን ጫካ ስወጣ ነው" የሰላም ተጓዥ ሙልጌታ አማሩ መገርሳ

Your browser doesn’t support HTML5

ሙልጌታ አማሩ መገርሳ የፊልም ጥበብ ባለሙያ እና የሰላም ተጓዥ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ዓድዋ በእግሩ በመጓዝ ለጉዞ ዓድዋ መጸነስ ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ ሁሌም በእግሩ መጓዝ የሚወደው ይህ ወጣት ከደቡብ አሜሪካ ጫፍ እስከ ሰሜን አሜሪካ የሚያደርሰውን ግዙፉን ፓን አሜሪካን ሃይዌይ(ጎዳና)ተከተሎ በእግሩ ከአርጀንቲና ጀምሮ ሃገራትን አቋርጦ ፓናማ ላይ በኮቪድ 19 ምክንያት ለማረፍ ተገዷል፡፡