ጥምቀት በጎንደር

Your browser doesn’t support HTML5

የጥምቀት በዓል ቁጥራቸው ከወትሮው እጅግ የበዛ ተሳታፊዎች በተገኙበት በተለይ በታሪካዊቷና ጥንታዊቷ ጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ ከታደሙት የአካባቢውና ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ጎንደር ከገቡ ምዕመናንና ጎብኝዎች በተጨማሪ ሰሞኑን ከዓለም ዙሪያ ወደ ትውልድ ሃገራቸው ከገቡ ኢትዮጵዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ መካከልም በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ መገኘታቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
“በኮቪድ-19 እና በተሳሳቱ መረጃዎች ምክንያት የውጭ አገር ጎብኝዎች ቁጥር መቀነሱን” የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የእስራኤልና የኤርትራ አምባሳደሮች እንደዚሁም ሌሎች እንግዶች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።