በእስር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ተለቀቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር ክልል አዋሽ 7 በእስር ላይ የነበሩት የአውሎ ሚዲያ እና የኢትዮፎረም ጋዜጠኞች ተለቀቁ።የኢትዮፎረም እና የአውሎ ሚዲያ 4 ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ5 ሺህ ብር ዋስትና በትናንትናው ዕለት የተፈቱ ሲሆን የአውሎ ሚዲያ ሌሎች 10 ባልደረቦች ደግሞ ከሳምንት በፊት ተፈትተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡