ኢትዮጵያ 1ኛ በመሆን ተመረጠች
Your browser doesn’t support HTML5
የፓስፊክ ቀጠና የጉዞ ፀሐፍት ማኅበር ኢትዮጵያን በአርኪዎሎጂካል ቦታዎች ዘርፍ መታየት ከሚገባቸው ሃገራት መሃከል አንደኛ አድርጎ መርጧል፡፡ በተመሳሳይም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የቱሪዝም መሪዎች አንደኛ በመሆን አሸናፊ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሚኒስቴር አማካሪ የሆኑትን አቶ ወርቅነህን አክሊሉ እና የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሰለሺ ግርማን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል፡፡