ከሙስሊም … ኮሚቴ በአቶ ዓሊ መኪ ላይ ተፈረደ

  • መለስካቸው አምሃ

ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በአቶ ዓሊ መኪ በድሩ ላይ በሌሉበት የ15 ዓመት ፅኑ እሥራት ፈርዷል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ከሙስሊም ኮሚቴ በአቶ ዓሊ መኪ ላይ ተፈረደ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በአቶ ዓሊ መኪ በድሩ ላይ በሌሉበት የ15 ዓመት ፅኑ እሥራት ፈርዷል፡፡

አቶ ዓሊ ቀደም ብሎ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ታስረው መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተለቅቀው ነበር፡፡

የችሎቱ ሂደት የተካሄደው በዝግ ቢሆንም የአሁኑ ውሣኔ ላይ እንዴት እንደተደረሰ ጠበቃቸው አቶ ተማም አባቡልጉ ለቪኦኤ አስረድተዋል፡፡

አቶ ዓሊ መኪ በድሩም ለቪኦኤ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የመለስካቸው አምሃን የፍርድ ቤት ውሎ ዘገባና ከአቶ ዓሊ መኪ በድሩ ጋር የተደረገውን ቃለ-ምልልስ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡