በሌላ በኩል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሦስተኛ ፓትርያርክ የሆኑት አቡነ እንጦንዮስ ከኃላፊነታቸው ተነስተው የቁም እስረኛ ከሆኑ 15 ዓመታት መቆጠሩ ይነገራል።
በኤርትራ የአዲሱ ፓትረያርክ በዓለ ሲመት ተከናወነ
Your browser doesn’t support HTML5
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትናንት ሰኔ 6 ቀን 5ኛ ፓትረያርኳን በታላቅ ድምቀት ሾማለች። በዚህ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሃይመኖት አባቶች፤ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ የኤርትራ ገዳማት ተውካዮች በተገኙበት ሥነ-ስርዓት ላይ ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ቤተ ክርስትያንና ህዝብን በቅንነት ለማገለገል ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።