በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሣይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር መረራ ጉዲና የሥራ ኮንትራት መቋረጥ ከትምህርት ክፍሉ ሊቀመንበር ተቃውሞ ገጥሞታል።
አዲስ አበባ —
Your browser doesn’t support HTML5
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሣይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር መረራ ጉዲና የሥራ ኮንትራት መቋረጥ ከትምህርት ክፍሉ ሊቀመንበር ተቃውሞ ገጥሞታል።
“…በዚህ ሁኔታ በኃላፊነቴ መቀጠሉ ከሞራል አንፃር ተቀባይነት የሉም…” ያሉት የዚሁ የፖለቲካ ሣይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ሊቀመንበር ዶክተር ካሣሁን ብርሃኑ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል።
“…የዩኒቨርሲቲው ውሣኔ ፖለቲካዊ ነው…” ያሉት ዶክተር መረራ ጉዲና በበኩላቸው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።
ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡