ከኢትዮጵያ በቀን ግማሽ ሚሊየን በርሜል ውኃ ለጅቡቲ
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያና ጂቡቲ በድንበር ተሻጋሪ ውሃ ልማትና ኢንቨስትመንት ላይ መከሩ። የኢትዮጵያና ጂቡቲ ከፍተኛ አመራሮች በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን የሚገኘውን የኢትዮ - ጂቡቲ ድንበር ተሻጋሪ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። በፕሮጀክቱ አሉ የተባሉ ክፍተቶች የተገመገሙ ሲሆን የጂቡቲ ባለሃብቶች በሶማሌ ክልል መዋዕለ ነዋያቸውን በሚያፈሱበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል።