በካመሩን የእግር ኳስ ሜዳ በተፈጠረ መረጋገጥ የሞትና መቁሰል አደጋ ደረሰ

Your browser doesn’t support HTML5

በካመሩን የአፍሪካ ዋንጫ ግጥሚያ እየተካሄደበት በነበረበት የእግር ኳስ ሜዳ በተፈጠረ መረጋገጥ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ 38 ስዎች ለጉዳት ተዳርገዋል።
ችግሩ የተከሰተው በካሜሩን እና ኮሞሮስ መሃከል ሊካሄድ የነበረውን ግጥሚያ ለመመልከት ኦሌምቤ ወደ ተሰኘው የእግር ኳስ ሜዳ ይገቡ የነበሩ ደጋፊዎች ቁጥር ሥርዓት ከሚያስከብሩ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ፖሊሶች በልጦ ከፍተኛ በመሆኑ በተፈጠረ ግርግር መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ካሜሩን እና የአፍሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርመራ እንዲካሄድ አዘዋል።
ሞኪ ኤድዊን ኪንዛካ፣ ከያውንዴ ያደረሰን ዘገባ ነው።