የአማራ ክልል የሰዓት እላፊውን አላላ
Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲከፈቱና ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ በከፊል እንዲሻሻል መወሰኑን የክልሉ መንግሥት ዛሬ አስታውቋል።
ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይትን በተመለከተ የክልሉ መንግሥት ያለው አቋም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።