ፌስቡክ መረጃን ለማጣራት እጠቀምበታለኹ ያለው "የማኅበረሰብ ማስታወሻ" ምንድን ነው?
Your browser doesn’t support HTML5
የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ትሬድ ማኅበራዊ ብዙኀን መገናኛዎችን የሚያስተዳድረው ሜታ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ የሚተላለፉ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስ፣ ኤክስ የቀድሞ ቲውተር ማኅበራዊ የትስስር ገጽ እንደሚያደርገው የማኅበረሰብ ማስታወሻዎችን እንደሚጠቀም አስታውቋል። ለመኾኑ፣ ሜታ መረጃን ለማንጠር እጠቀምበታለኹ የሚለው ይኸው የማኅበረሰብ ማስታወሻ ምንድን ነው? ሐሰተኛ መረጃን የመዋጋት ዐቅሙስ ምን ያህል ነው?