"ሞዴል ዩኤን" ወይም "አምሳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት"፦ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዲፕሎማሲን እንዲማሩ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የትኩረት አቅጣጫ በኾኑ የልማት ግቦች ላይ ግንዛቤን እንዲያዳብሩ የሚደረግ የውይይት እና የክርከር መርሐ ግብር ነው፡፡
መርሐ ግብሩ፣ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በብዙ ሀገራት የተዘረጋ መድረክ ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የኾነው ጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ፣ በየዓመቱ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች ለመጡ ተማሪዎች መርሐ ግብሩን ያዘጋጃል፡፡በዘንድሮው መርሐ ግብር፣ 45 ኢትዮጵያውያን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከባላፈው ቅዳሜ የካቲት አንድ 2017 ዓ.ም አንስቶ ሁለት ሳምንት በሚዘልቀው መርሃግብር ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
የመርሐ ግብሩ አስተባባሪ፣ በትምህርት ላይ የሚሠራው "ኦል ፋውንዴሽን" ሲኾን፣ የተቋሙ መሥራች እና የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ኑርሑሴን ሐሰን ሑሴን፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡: