የቀድሞ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐቶች በጆርጂያ ክፍለ ግዛት ተጀምሯል

  • VOA News

ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ፎቶ በጥቁር ጨርቅና በአበባ በአጌጠ ፎቶ ማስቀመጫ፣ አትላንታ ጆርጂያ ካፒቶል ሕንጻ ውስጥ የተዘጋጀ/ እንደ አዎሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 3 ቀን 2025 ዓ.ም

ባለፈው ሳምንት እሁድ በአንድ መቶ ዓመታቸው በሞት የተለዩት የ39ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት መርሐ ግብሮች በኖሩበት በጆርጂያ ክፍለ ግዛት ትላንት ቅዳሜ ተጀምሯል።

ለስድስት ቀናት በሚዘልቀው የሽኝት ሥነ ሥርዓት አስከሬናቸው ትላንት በትውልድ ከተማቸው በሚገኘው የቤተሰባቸው መኖሪያ እና እርሻ በኩል በክብር አጀብ አልፎ አትላንታ ከተማ ወደሚገኘው የካርተር ፕሬዝደንታዊ ማዕከል ለሐዘንተኞች እና አድናቂዎቻቸው ስንብት ተቀምጧል።

በመቀጠል ወደ ዋሽንግተን ይሸኝ እና በተመሳሳይ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሕንጻ " ካፒቶል ሮተንዳ" አዳራሽ በክብር አርፎ ስንብት ይደረጋል። ሐሙስ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ በዋሽንግተን ብሔራዊ ካቴድራል የሽኝት መርሐ ግብር ይከናወናል።

ፋይል - የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር ሰሜን ኮሪያ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ ዋሽንግተን ውስጥ ለባልሥጣናት ገለጻ አድርገው ከዋይት ሃውስ ሲወጡና ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ። ጂሚ ካርተር ፣ የሰሜን ኮሪያ ቀውስ እንደሚያበቃ ለጋዜጠኞቹ ተናግረው ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሰኔ 19 ቀን 1994 ዓ.ም.

/የአሜሪካ ድምጹ ኬን ፋራቦ የኖቤል የሰላም ተሸላሚውን ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ሕይወት እና የሕዝባዊ አገልግሎት ታሪክ በሚመለከት ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዐቶች በጆርጂያ ክፍለ ግዛት ተጀምሯል